አዲስ ምዝገባ

 • አመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው 2 (ሁለት) ጉርድ ፎቶግራፍ፤
 • አመልካቹ በአስተዳደሩ ውስጥ ከሚኖርበት ወረዳ የታደስ የነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት፤
 • በግብር ሰብሳቢው መስሪያቤት የተሰጠው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ እና
 • አመልካቹ በአሁኑ ወቅት በመደበኛ ንግድ ስራ ላይ ወይም ሌላ ማንኛውም ስራ ላይ ያልተሰማራ ስራ አጥ መኒኑን በአስተዳደሩ ውስጥ ከሚኖርበት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ማስረጃ፡፡
 • አመልካቹ ይህን ደንብና ደንቡን ተከትሎ የሚወጣውን መመሪያ አክብሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን በሚያቀርበቀው ማመልከቻ ላይ ማረጋገጥ ይኖርበታል
 • አመልካቹ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተነሳው 2 (ሁለት) ጉርድ ፎቶግራፍ፤

እድሳት

 • መደበኛ ባልሆነ ንግድ ሥራ ላይ ለተሰማራ ማንኛውም ሰው የተሰጠውን ደረት ላይ ተንጠልጣይ የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ የበጀት አመት ካበቃ በኋላ ባለው 6 ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም ሐምሌ 1 ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን ድርስ ከግብር አስከፋይ መስሪያ ቤት ክሊራንስ በማቅረብ እና በዚህ ደንብ አንቅፅ 11 ንዑስ አንቅፅ 2 መሠረት ተገቢው ክፍያ ተከፍሎ በየአመቱ በመዝጋቢው አካል መታደስ አለበት።
 • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ደረት ላይ ተንጠልጣይ የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያውን ሳያድስ የቀረ ሰው በሚቀትሉት ስድስት ወራት ውስጥ ማለትም ከጥር 1 ቀን እስከ ሰኔ 30 ድረስ ባሉት ወራት የመደበኛ የሽግግር ፈቃድ ወይም መታወቂያ ማሳደሻ ክፍያ አጥፍ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ፈቃዱን ማደስ ይቻላል።
 • በዚህ አንቀፅ መሠረት የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያውን ያላሳደሰ ሰው ከመዝገብ ይሰረዛል። ተመዝጋቢው የተሰጠውን ደረት ላይ የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ መመለስ አለበት። ሣይመለስ ቢቀር በእጁ እንዳለ እንደተሰረዘ ይቆጠራል።

የጠፋ/የተበላሸ

 • መደበኛ ያልሆነ ንግድ ሥራ ምዝገባ ያደረገ ማንኛውም ሰው የተሰጠው የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ የጠፋበት ወይም የተበላሸበት ከሆነ ቀደም ሲል ለሰጠው የወረዳ ጽ/ቤት በጸሑፍ በማመልከት ምትክ የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ ማግኘት ይችላል
 • የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ የተበላሸበት ማንኛውም ሰው ምትክ እንዲሰጠው ሲጠይቅ የተበላሸውን ይምልሳል።
 • ወረዳው ማመልከቻ ሲቀርብለት ለጠፋው ወይም ለተበላሸው የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታወቂያ በዚህ ደንብ የተመለከተውን ክፍያ በማስከፈል ምትክ ፈቃድ ወይም መታውቂያ ይሰጣል።

የፈቃድ ማሻሻያ

 • ማንኛውም ሰው ተመዝግቦ የሚሰራውን የንግድ መስክ አይነት መለውጥ ወይም ማሻሻያ ከፈለገ የተመዘገበበት ወረዳ ጽ/ቤት በመቅረብ በቢሮው የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት የሚሰራውን የንግድ መስክ ዓይነት መለወጥ ወይም ማሻሻል ይችላል፡፡
 • የምዝገባ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ስለማቅረቡ እና ተቀባይነት ስለማግኘቱ የወረዳው ጽ/ቤት ማረጋገጫ መስጠቱንና ተቀባየነት ያገኘበትን ቀን፣ ስለ ምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ በዝርዝር መግለጹን ለአመልካቹ እና ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ የጽሑፍ ማረጋገጫ ካልተሰጠ በስተቀር ያቀረበው የምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ እንደተለወጠ ወይም እንደተሸሻለ አይቆጠርም፡፡

የአድራሻ ለዉጥ

 • ማንኛውም ሰው የንግድ ስራው ለማካሄድ ከተመዘገበበትና ከተመደበበት የሥራ ቦታ አከባቢ ወደ ሌላ የሥራ ቦታ አከባቢ ለመለወጥ ከፈለገ በዚህ ደንብ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 8 ንኡስ አንቀጽ 2 ያደረገውን ምዝገባ መሰረዝና ከወረዳው ጽ/ቤት የተሰጠውን ደረት ላይ የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ ለወረዳው ጽ/ቤት፤ በቀጣይ መሸኛ ወረቀት በመውስድ ወደመረጠው አከባቢ የሚገኝ የወረዳ ጽ/ቤት መሸኛውን በማቅረብ ሌላ ደረት ላይ የሚንጠለጠል የሽግግር ጊዜ ፈቃድ ወይም መታውቂያ በመውሰድ መነገድ ይችል ፤
 • የምዝገባ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ስለማቅረቡ እና ተቀባይነት ስለማግኘቱ የወረዳው ጽ/ቤት ማረጋገጫ መስጠቱንና ተቀባየነት ያገኘበትን ቀን፣ ስለ ምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ በዝርዝር መግለጹን ለአመልካቹ እና ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ ይህ የጽሑፍ ማረጋገጫ ካልተሰጠ በስተቀር ያቀረበው የምዝገባው ለውጥ ወይም ማሻሻያ እንደተለወጠ ወይም እንደተሸሻለ አይቆጠርም፡፡

የቅሬታ ማቅረቢያ

ንግድ ፍቃድ ባለመኖር ምክንያት የተዘጋ ድርጅት ለማስከፈት